Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዝቋላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
  • Address አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0922936728
  • Website
  • Deadline30 Dec 2024, 11:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle Battery

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዝቋላ የመ/ደረጃ/ ሆስፒታል በ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት እቃዎች ፣ የእስቴሽነሪ እቃዎች ፣ ህትመት ፣ የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ፣ የመኪና ጎማ ፣ የመኪና እስፔር ፓርቶች ፣ የመንግስት ሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ 2017 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዝቋላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


የአገር  አቀፍ  ግልፅ  ጨረታ  ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዝቋላ የመ/ደረጃ/ ሆስፒታል በ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት እቃዎች ፣ የእስቴሽነሪ እቃዎች ፣ ህትመት ፣ የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ፣ የመኪና ጎማ ፣ የመኪና እስፔር ፓርቶች ፣ የመንግስት ሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ 2017 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ከ200,000 ሺ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ እና መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ለመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና ሌላም መረጃ ፎቶኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በሁለት ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ ማቅረብ አለባቸው ።
  6. የሁሉንም የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተቋሙ ካስቀመጠው እስፔስፍኬሸን ውጭ በራሱ ጊዜ እስፔስፍኬሽን የጨመረና የቀነሰ ወይም ያስቀመጠ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ለ15 ተከታታይ ቀናት በዝ/የመ/ደ/ሆስፒታል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እና በ16ኛው ቀን ከ2፡00 እስከ 5፡30 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በማስገባት በዚያው ቀን 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በዝ/ወ/የመጀ/ደ/ሆስፒታል በግልፅ ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ማስያዝ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች ከሚወዳደሩበት ሰነድ ላይ ከአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ያደረገ ከጨረታው (ከውድድሩ) ውጭ ይሆናል።
  11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዕቃ ውድድሩ በሎት /በጠቅላላ ድምር/ ስለሆነ የሚሞሉት የጨረታ ሰነድ አንዱም ዕቃ ሳይሞሉ ከቀሩ ከጨረታው /ከውድድሩ/ ውድቅ ይሆናሉ።
  12. የደንብ ልብስ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ተቋሙ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት መሆኑ መታወቅ አለበት።
  13. ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆኑ የጨረታውን ውል ማስከበርያ ያቀረቡትን የጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ በሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ8 ቀን ውስጥ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  14. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉቸውን እቃዎች ቦታው ድረስ ማለትም ዝ/ወ/ የመጀ/ደ/ሆስፒታል ድረስ በማምጣት ዕቃዎች አስረክቦ ራሱ ሂሳቡን ማወራረድ ይኖርበታል።
  15. መ/ቤቱ በጨረታው ዙሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግስት ስራ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰአት በተመሳሳይ ጊዜ ይከፈታል።
  17. ለበለጠ መረጃ 0922936728/0910188787 የግል ስልከ ያስቀመጥነው የቢሮ ስልክ የሚሰራ ስለሌለ መሆኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በአማራ  ብሄራዊ  ክልላዊ  መንግስት  የዝቋላ  የመ/ደረጃ/  ሆስፒታል

Save Tender