በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን የሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን በ2017 ዓ.ም የተለያዩ መጠን ያላቸው ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን የሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን በ2017 ዓ.ም የተለያዩ መጠን ያላቸው ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሰርተፍኬት እና የታከስ ከፋይነት ማረጋገጫ /ቲን/ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የእቃ ወይም የአገልግሎት አቅራቢነት ምስክር ወረቀት በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ እየከሉ ከወ/ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 13 የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ይህ ማስታወቁያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50000 /ሃምሳ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች አንዱን እቃ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው ዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ በመሙላት በወላይታ ሶዳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ አገልግሎት ኮርፖሬሽን ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን እቃዎች አስፈላጊውን ውለታ በመፈፀም ሙሉ በሙሉ ወሶዳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ድረስ በመቅረብ ገቢ ሲያደርጉ ክፍያ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ አቀራረብን በተመለከተ 1 /አንድ/ ኦርጅናል እና 1 /አንድ/ ኮፒ ተዘጋጅቶ በጨረታ ሣጥን በዕለቱ በመጨመር በታሸጉ ፖስታዎች ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0465512333/0913341782/0912138978 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው:፡
የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን
