የደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የሚገለገልባቸውን መኪኖች ለአንድ ዓመት በሚቆይ ኮንትራት በሳውላ ከተማ ወይም በወላይታ ሶዶ ከተማ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ
የተሽከርካሪ ጥገና ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የሚገለገልባቸውን መኪኖች ለአንድ ዓመት በሚቆይ ኮንትራት በሳውላ ከተማ ወይም በወላይታ ሶዶ ከተማ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በትራንስፖርት ሚኒስቴር ወይም በደ/ኢት/ክ/መ/ትራንስፖርት ቢሮ ወይም በሲ/ብ/ክ/መ/ትራንስፖርት ቢሮ ደረጃ 3 እና በላይ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመ/ቤቱ ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጥገና አገልግሎት በሚያቀርቡት ላይ የተጨማሪ አሴት ታክስ (VAT) በማካተት ኦሪጅናል የቴክኒካልና የፋይናሻል ሰነዶችን ለየብቻ እንዲሁም ኮፒ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ/ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በደቡብ ኢትዮጵያ ክፍት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት/ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በቂና ምቹ የጥገና አገልግሎት መስጫ ቦታ ያላቸው መሆኑን ለጨረታ ኮሚቴዎች ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የጥገና አገልግሎት ማግኘት የሚፈልገው በሳውላ ወይም በወላይታ ሶዶ ከተማ ብቻ ነው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0911050428/0916108644 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ
