Tender Detail

Tender Details

  • Company አላጌ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ
  • Address በአዲስ አበባ 22 ማዞሪያ በአከሱም ሆቴል ገባ ብሎ አዲስ ሕይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘው የኮሌጁ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116189677
  • Website
  • Deadline27 Dec 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የአላጌ ግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን አቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

አላጌ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ


የግልፅ  ጨረታ  ማስታወቂያ

 

የአላጌ ግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን አቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

         ሎት 1 የሠራተኛ ደንብ ልብስ ግዥ

         ሎት 2 የእንስሳት መኖ ግዥ

         ሎት- 3 የእርሻ ትራክተር ኪራይ

በዚሁ መሠረት በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት ላይ ለመመዝገባቸው የዌብ ሳይት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ወረቀት፤ በመስኩ የተሰማራበት የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት በጨረታው እንዲሳተፉ የሚል የድጋፍ ደብዳቤ ፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ፤ የታክስ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር : ከሆኑ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሠነዱ ላይ የተጠቀሰውን ገንዘብ መጠን በሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች
  5. አላጌ ግብርና ቴከኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ በመምጣት ዕቃ ግ/ቤት ማስረከብ አለባቸው።
  6. ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቀንና ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል 16ኛ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  7. ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በአዲስ አበባ 22 ማዞሪያ በአከሱም ሆቴል ገባ ብሎ አዲስ ሕይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘው የኮሌጁ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ዘወትር በሥራ ሠዓት በግንባር ቀርበው ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

የበለጠ መረጃ ቢያስፈልግዎት በስልክ ቁጥር 0116189677 አዲስ አበባ ወይም 0461165053/046 1165005 ወይም 0903337868 አላጌ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ

 

አላጌ  ግብርና  ቴክኒክና  ሙያ  ትምህርትና  ሥልጠና  ኮሌጅ

Save Tender