በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa Driver and Vehicle Licensing and Control Authority (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አሽተሽፍቁባ /መግዳ/ 2017/ 002
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ሎት 1. የደንብ ልብሶች
ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 4. የመንጃ ፍቃድ ካርድ ፕሪንተር፣ ሪቫን፣ ላምኔሽንና መንጃ ፍቃድ ካርድ
ሎት 5. የማስታወቂያና የህትመት እቃዎች
ሎት 6. የመኪና ዕቃዎች
ሎት 7. የአይሲቲና የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች
ሎት 8. ፍሪጅና ቴሌቪዥን
ሎት 9. ጀኔሬተር
ሎት 10. ፈርኒቸርና ሌሎች ቁሳቁሶች
ሎት 11. የእድሳትና ጥገና ዕቃዎች
- ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና መስሪያ ቤት መክሊት ህንፃ 8ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 804 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ገዝታችሁ መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት ለእያንዳንዱ ሎት በተናጥል (ለየብቻ) በባንክ የተረጋገጠ CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ለሎት 1፣ 2፡ 3፣ 5፣ 6፣ 8 እና 11 ለእያንዳንዳቸው በተናጥል የ10,000 ብር (አስር ሺህ) CPO
- ለሎት 4 የ500,000 ብር (አምስት መቶ ሺህ ብር) CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ለሎት 7 የ200,000 ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር) CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ለሎት 9 እና 10 ለእያንዳንዳቸው በተናጥል የ100,000 ብር (አንድ መቶ ሺህ ብር) CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ባለስልጣን መስሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ውይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከጐላጐል ታወር ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ መክሊት ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር (708)፤ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011- 667-23-36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባስስልጣን
