በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ የመኪና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ፕላንና ልማት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ የመኪና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
- የአቅራቢነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
- የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬትና መለያ ቁጥር ያለው
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የግብር ከፋይነት ማስረጃ የሚያቀርብ
- የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፕስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር ከፍለው መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5000 በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ለእያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማጠቃለል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ፕላንና ልማት ቢሮ ግዥ ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 209 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በሲዳማ ብ/ክ/ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ
