Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline31 Dec 2024, 3:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Works

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ -1 ጠቅላላ የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ ወይም ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GWWC-1/GC-1) የሆኑ የአገር ውስጥ እና የአገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ /Airsde/ የውሃ መገኛ ልማት እና የላንድ-ስኬፒንግ ፕሮጀክት ስራን በዲዛይን እና ግንባታ የውል ዓይነት (Design & Construction Turn-Key Bases) ለማሰራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


ድጋሚ  የወጣ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር : SSNT-T510

 

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ -1 ጠቅላላ የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ ወይም ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GWWC-1/GC-1) የሆኑ የአገር ውስጥ እና የአገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ /Airsde/ የውሃ መገኛ ልማት እና የላንድ-ስኬፒንግ ፕሮጀክት ስራን በዲዛይን እና ግንባታ የውል ዓይነት (Design & Construction Turn-Key Bases) ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

  1. የፕሮጀክቱ ዲዛይን እና ግንባታ ሥራው በ210 ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ አለበት።
  2. ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሸን ባለስልጣን ለ2016 ዓ.ም የታደሰ በጠቅላላ የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ ደረጃ-1 ወይም ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ-1 (GWWC-1/GC-1) የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-7510 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኃላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፣-

ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ስልክ ቁጥር፡ +25111-517-89-18

ኢ-ሜይል: ESAYASIS@ethiopianairlines.com

 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Save Tender