በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ የትምህርት እና ስልጠና መርጃ እቃዎች፣ የተለያየ የህሙማን ቀለብ፣ የተለያዩ የቤት ግንባታ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች እና የተለያዩ አላቂ የቁሳቁስና ፕሮፓጋንዳ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢፌዴሪ ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ የትምህርት እና ስልጠና መርጃ እቃዎች፣ የተለያየ የህሙማን ቀለብ፣ የተለያዩ የቤት ግንባታ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች እና የተለያዩ አላቂ የቁሳቁስና ፕሮፓጋንዳ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የቫት ተመዝጋቢ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ደዴሳ ምዕ/ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ግዥ ዴስክ ቢሮ ቀጥር 06 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ CPO በየዘርፋቸው እንደሚከተለው ሲሆን ለአላቂ የፅህፈት መሳሪያ 1,399.69 /አንድ ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር ከ69/100/ ብቻ፤ ለት/ት መረጃ ዕቃዎች ብር 6,322.69 /ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ሁለት ብር ከ69/100/ ብቻ፤ ለተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች 6,814.26 /ስድስት ሺህ ስምንት መቶ አስራ አራት ብር ከ26/100/ ብቻ፤ ለተለያዩ የቤት ግንባታ ዕቃዎች 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ፣ ማስያዝ ይኖርባችኃል፡፡
- ጨረታው ማክሰኞ ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደዴሳ ምዕ/ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በቅደም ተከተል ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ክልል ፡- ኦሮሚያ ዞን፦ ምስራቅ ወለጋ ወረዳ፦ ዲጋ ቀበሌ፡- ጉደቱ አርጆ ዲዴሳ ካምፕ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-22-27-04-01 ወይም 09-00-81-85-05 መደወል ይቻላል፡፡
በኢፌዴሪ ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል
