Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት
  • Address ባህር ዳር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0582266077
  • Website
  • Deadline08 Jan 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Audio Visual, Photography And Filming Service And Equipment

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የፎቶ ካሜራ እና የፎቶ ካሜራ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት


የግልፅ  ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  ARARI /01/03/2017

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የፎቶ ካሜራ እና የፎቶ ካሜራ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው::
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 በግንባር በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ሆኖ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ሲሆን ለDron Camera ግዥ ብቻ መወዳደር የሚችሉ የጉምሩክ ዲክለራሲዮን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  7. ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ተያይዟል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋውን 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ቢሮ ቁጥር 119 ደረሰኝ በማስቆረጥ ማስያዝ አለባቸው::
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 120 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 31ኛው ቀን የሚውለው በበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ኦፊሰሮች ከፍል ቢሮ ቁጥር 120  በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፤ 31ኛው ቀን በበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታ አሸናፊ ከሆነ ያሸነፉበትን 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 120 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582266077 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር-0583205074 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በአማራ  ብሔራዊ  ክልላዊ  መንግስት  የግብርና  ምርምር  ኢንስቲትዩት

ባህር ዳር

Save Tender