Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
  • Address ሶዶ : ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0461804426
  • Website
  • Deadline23 Dec 2024, 3:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicles Rent

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ የመንገድ ጥገና እና ግንባታ ሥራ ፐሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን መገልገያዎችን ተሽከርካሪ ማለትም፤ የሰርቪስ እና ጭነት አገልግሎት የሚሰጡ አይሱዙ እና የውሃ ቦቴ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት


የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  ሶዶ  ዲስትሪክት  001/2017

 

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ የመንገድ ጥገና እና ግንባታ ሥራ ፐሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን መገልገያዎችን ተሽከርካሪ ማለትም፤ የሰርቪስ እና ጭነት አገልግሎት የሚሰጡ አይሱዙ እና የውሃ ቦቴ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ የሥራ የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንስ ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ ‹‹አሪጅናል›› እና ‹‹ኮፒ›› በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሶዶ ዲስትሪከት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሠነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው መስፈርቱን ለሚያሟላ ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  6. በጨረታው የሚቀርቡ ፣ የውሃ ቦቴዎች 13,000 ሊትርና ከዚያ በላይ እንዲሁም አይሱዙዎች 35 ኩ/ል እና ከዚያ በላይ መጫን የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ የአይሱዙ ተሽከርከሪ የስሪት ዘመን እ.አ.አ 2008 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸዉ፡፡ ሁሉም ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ጌጅ እና ኪ/ሜትራቸው በትክክል የሚሰሩ መሆን አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም::
  8. ተጫራቾች በጨረታ ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም እንዲሁም ሌሎች ተጫራቾች በሚሞሉት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  9. ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገደ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461804426 ሶዶ ዲስትሪክት ፋይናንስና ሎጀስቲክስ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡- የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

 

የደቡብ  ኢትዮጵያ  መንገዶች  ባለሥልጣን  ሶዶ  ዲስትሪክት  ጽ/ቤት

Save Tender