የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የ2016 እና የ2017 በጀት ዓመት አመታዊ የደንብ ልብስ በሀገር ውስጥ ጨረታ በግልጽ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
Ethiopian Athletics federation (የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን)
በድጋሚ የወጣ የደንብ ልብስ ግዥ ግልፅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የ2016 እና የ2017 በጀት ዓመት አመታዊ የደንብ ልብስ በሀገር ውስጥ ጨረታ በግልጽ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በዚሁ መሠረት ፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደስ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ::
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር የሚያቀርቡትን የደንብ ልብስ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል::
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ከማስገባታቸው በፊት በፌዴሬሽኑ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ የደንብ ልብስ ዓይነት፣ ብዛትና ሳምፕል በመውሰድ በቀረበው ሰነድ ላይ ዋጋቸውን ሞልተውና አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ለእያንዳንዱ ደንብ ልብስ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ ከቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሣጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ከቢሮ መዋሰድ ይኖርባቸዋል::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
ለበለጠ መረጃ ፡- 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
ፋክስ - 0116-45-08-79
ፖ.ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
