በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/ አስ/ቡድን በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ላሉ የመንግስት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫ/ስፔርፓርት እና በወረዳው ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የቢሮ ቋሚ ዕቃ/ፈርኒቸር ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/ አስ/ቡድን በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ላሉ የመንግስት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫ/ስፔርፓርት እና በወረዳው ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የቢሮ ቋሚ ዕቃ/ፈርኒቸር ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ግዥው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከ29/03/2017 ዓ/ም እስከ 13/04/2017 ዓ/ም በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር እሁድ ቅዳሜን ጨምሮ እስከ 11:30 በመምጣት የማይመለስ 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ14/04/2017 ዓም 8፡00 ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ህጋዊ ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት እና የሚታሸግበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ/ካላደር የሚዘጋው ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 8፡00 ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች/ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ ይከፈታል::
- የጨረታ አሸናፊው የመኪና መለዋወጫ /ስፔር ፓርትን/ ጎንደር ከተማ ማቅረብ የሚችል ሲሆን የቢሮ ቋሚ ዕቃ/ፈርኒቸር ግን በየዳ ወረዳ ድል-ይብዛ ከተማ በስድስቱ ንበረት መጋዘን ማቅረብ የሚችል እና ማውረጃ እና መጫኛ በተጫራቹ መሸፈን የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የመኪና መለዋወጫን /ስፔር ፓርትን/ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም ድረስ ውል ወስደው ማቅረብ የሚችሉ እና በተጠየቀ በአምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ኦሪጅናል የመኪና መለዋወጫን /ስፔር ፓርትን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሰረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚመታው ማህተም ከንግድ ፈቃዱ ጋር ቀጥተኛ /ተዛማጅ የሆነ መሆን አለበት።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0918352228 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ ገን/ጽ/ቤት
