የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ከንቲባ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚሰጡ ካሜራ (5D Orginal mark 4 Camera: Godox spot: Tripod:Camera Bag and Sandisk memory) ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ከንቲባ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚሰጡ ካሜራ (5D Orginal mark 4 Camera: Godox spot: Tripod:Camera Bag and Sandisk memory) ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር ) በባንከ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ የተረጋገጠ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ::
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ ልማ/ መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡15 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
