የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከአዲስ አበባ 450 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በደቡብ ክልል ለሚገኘው ግልገል ጊቤ 3ኛ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የአሳንሰር (ሊፍት) አቅርቦትና ገጠማ እገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- EEP/GOP/NCB/09/2017
- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከአዲስ አበባ 450 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በደቡብ ክልል ለሚገኘው ግልገል ጊቤ 3ኛ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የአሳንሰር (ሊፍት) አቅርቦትና ገጠማ እገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በግዥ ኤጀንሲው ድረ-ገጽ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታብረት አጠገብ ካለው አቢሲኒያ ባንከ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይል እና ፋይናንስ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በግዥ ክፍል ህንጻ ምድር ቤት ጀነሬሽን ኦፕሬሽን ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የአቅርቦት እና አገልግሎት ግዥ በሚመለከት የቴክኒካል እና የፋይናንሻል የመወዳደርያ ሠነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/GOP/ NCB/09/2017 የሚል ምልክት በማድረግ 1 (አንድ) ኦሪጂናል እና 1 (አንድ) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ከዚህ በታች በተገለጸው ሠንጠረዥ መሰረት የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን ብር |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የአሳንሰር (ሊፍት) አቅርቦት እና ገጠማ አገልግሎት ግዥ |
ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) |
ታኅሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት |
ታኅሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት |
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር ፡- 011-5-57-42-95 መደወል ይችላሉ፡፡
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
