ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ISO /INTERNATIONAL ORGANZATION FOR STANDARDIZATION/ ትግበራ ሥራ ለማከናወን የሚረዳ በዚሁ ዘርፍ ሙያዊ እውቀት እና ከህሎት ያላቸውን አማካሪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሚ/ኮ/ግዥ/ን/አስ/0004/2017
ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ISO /INTERNATIONAL ORGANZATION FOR STANDARDIZATION/ ትግበራ ሥራ ለማከናወን የሚረዳ በዚሁ ዘርፍ ሙያዊ እውቀት እና ከህሎት ያላቸውን አማካሪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት የሚኖርባቸው ዋና ዋና ቅድመ ሁኔታዎች፣
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት ተመዝጋቢ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቴክኒካል ሠነድ እና የጨረታ መመሪያ ሠነድ ተያይዞ የቀረበ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሚድሮከ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን አጠገብ ኩዊንስ ህንጻ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 14 በመምጣት የማይመለስ ብር 1,000.00 / አንድ ሺህ / ብር በመክፈል መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /C.P.O/ በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታው ሰነድ ጋር ለብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴከኒካል ሠነዳቸውን አሪጅናል እና ኮፒ ለብቻ በፖስታ በማሽግ እና ፋይናንሻል ሠነድ አንድ ኦርጅናል ለብቻ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜ፣ እሁድ እና በዓላት ጨምሮ በተከታታይ ለ15 /አስራ አምስት/ ቀን አየር ላይ ከዋለ በኋላ ከ16ኛ /አሥራ ስድስተኛው/ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡15 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በታሸገ ፖስታ እና ማህተም በማሳረፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 23 84 29 እና 09 12 50 21 56 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
አዲስ አበባ
