የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ከዚህ በታች እስከ ሎት15 የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Defense Engineering Industry Corporation (የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ከዚህ በታች እስከ ሎት15 የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 - ጥሬ ዕቃዎች
ሎት 2 - ኬሚካሎች
ሎት 3 - ዘይት እና ቅባት ዕቃዎች
ሎት 4 - ቱልስ እና ኦግዝለሪ ዕቃዎች
ሎት 5 - የመካንካል ዕቃዎች
ሎት 6 - የኤሌክትሪካል ዕቃዎች
ሎት 7 - የቤልት ዕቃዎች
ሎት 8 - ማሽን ዕቃዎች
ሎት 9 - የኮንስትራክሽን ዕቃዎች
ሎት 10 - የፕሮጀከት ዕቃዎች
ሎት 11 - የፅህፈት ማሳሪያ ዕቃዎች
ሎት 12 - የሴፍቲ ዕቃዎች
ሎት 13 - የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 14 - ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ሎት 15 - የተሸከርከሪዎች ጎማ
በመሆኑም ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ለመግዛት ስለምንፈልግ ፤ ማንኛውም ተጫራች
በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በመንግስት ዕቃ ግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ የሆኑና ፡-
- የወቅቱን ግብር ያጠናቀቁ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT 15% ከፋይነት የተመዘገቡ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ዋና እና ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በሁለት ቅጅዎች ማቅረብ አለባቸው አንደኛው ቅጅ ላይ ኦርጅናል ቴክኒካል ዶከመንት እና ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶክመንት በማለት በሁለተኛው ቅጅ ላይ “ኮፒ” የሚል ምልክት እና ፖስታዉ ላይ ህጋዊ የሆነ ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ሰነዱም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት ዝርዝሩን ሞልተው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተገለፀው አድራሻ በተዘጋጀው ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ከ26/03/2017 እስከ 16/04/2017 ዓ.ም ድረስ መግዛት እና ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ 17/04/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ከእስፔሲፊኬሽን ውጭ የሆነ ዕቃ በሚያቀርቡ ተጫራቾች ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም በላይ በዚህ ምክንያት ለሚደርሰው ኪሣራ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጨረታ ሰነዱን እና የጨረታ ሳጥኑ የሚገኘው አምቦ ምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር በተዘጋጀው ጊዜያዊ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0919203368/0920944104/0969391969 ወይም +251-11-2-19-00-42 ይደውሉ፡፡
የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
