በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለአስተዳደሩ አገልግሎት እየሰጠ ያለው ሰርቨር የእስፔርፓርት እቃዎችና ኤሌክትሮኒክሶች በዚህ ማስታወቂያ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨ/መ/ቁ ፋ/ኢ/ልማት ቢሮ 002/2017
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለአስተዳደሩ አገልግሎት እየሰጠ ያለው ሰርቨር የእስፔርፓርት እቃዎችና ኤሌክትሮኒክሶች በዚህ ማስታወቂያ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
በዚሁ መሰረት ፡-
- በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- በተለይ ለሰርቨር ባትሪ እና UPS እቃዎች ግዥ ከአምራች ወኪል አከፋፋይ ፈቃድ ያለው
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ቁጥር 201 ቀርበው ብር 400.00 (አራት መቶ) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በጨረታ መክፈቻው እለት የጨረታ ሠነዱን በትክክል ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 201 በግልጽ ሲከፈት፤ ቀኑ በዓል ወይም የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 50,000 ብር (ሃምሳ ሺ ብር ) በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የስልክ ቁጥር 0928-11-80-00/0915-73-23-12
የድሬዳዋ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
