በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቸርችል ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት የደንብ ልብስ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፤ የህትመት ስራዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ባለሙያ፤ የልብስ ስፌት እና የጥገና መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቸርችል ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቸርችል ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት የደንብ ልብስ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፤ የህትመት ስራዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ባለሙያ፤ የልብስ ስፌት እና የጥገና መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ከገንዘብና ኢኮኖሚክ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ የእሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፤
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ 25,000.00 ብር ( ሃያ አምስት ሺ ብር) በእያንዳንዱ ሎት በድርጅቱ ስም ሲፒኦ በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በጥንቃቄ ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የያዘ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቸርችል ጤና ጣቢያ ግዥ ከፍል በአካል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 3፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ ቸርችል ጤና ጣቢያ አዳራሽ በግልፅ ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የካታሎግ ወይም ናሙና እስፔስፊኬሽን ማቅረብ አለባቸው፤
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0118265084
አድራሻ፡- ፒያሳ ቸርችል ሆቴል በታች ሊሴ ገ/ማርያም ት/ቤት ጀርባ
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቸርችል ጤና ጣቢያ
