Tender Detail

Tender Details

  • Company ጋርዱላ ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን ጊዶሴ
  • Address ጋርዱላ ዞን ግብርና መምሪያ ግቢ ውስጥ በስተግራ በኩል ፡ ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0939465386
  • Website
  • Deadline19 Dec 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Soil Fertilization

ጋርዱላ ሁለገብ ኅ/ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጋርዱላ ዞን ወረዳዎች ከተማ አ/አደሮች በያዝነው ነው ምርት ዘመን 2017 ዓ.ም ለአርጉባ ጣናኦ ፣ አፊያ፣ ሆልቴ፣ ቡሳ ባሶ እና ያይቤ ቀበሌ ለሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማራገፊያ ጣቢያዎች፣ የበልግና የመኸር እና ለበጋ መስኖ የአፈር ማዳበሪያ /ምጥን/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

ጋርዱላ ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን ጊዶሴ


የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2 2017

 

ጋርዱላ ሁለገብ ኅ/ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጋርዱላ ዞን ወረዳዎች ከተማ አ/አደሮች በያዝነው ነው ምርት ዘመን 2017 ዓ.ም ለአርጉባ ጣናኦ ፣ አፊያ፣ ሆልቴ፣ ቡሳ ባሶ እና ያይቤ ቀበሌ ለሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማራገፊያ ጣቢያዎች፣ የበልግና የመኸር እና ለበጋ መስኖ የአፈር ማዳበሪያ /ምጥን/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ለድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ መሠረት በማድረግ ለማጓጓዝ የሚፈልገዉ የማድረሻ ዋጋ በጠ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካኝ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋበዛል፡

በዚሁ መሠረት ፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው /ያላት፣
  2. ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል ምስክር የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  3. ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሥራው በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችል፣
  4. የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ማራገፊያ ጣቢያ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና ወይም መወዳደር አይችሉም፡፡
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ /cpo/ ብር /300,000/ /ሦስት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይይኖርባቸዋል፡፡
  6. በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈጸሙ በፊት ያሸነፈበትን የጭነት ማጓጓዣ ዋጋ 10 ፐርሰንት ለውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ያስይዛል፡፡
  7. ተጫራቾች የተሽከረካሪዎችን ዝርዝር ቢያንስ 2,400 /ሁለት ሺህ አራት መቶ/ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን የሠሌዳ ቁጥር፣ የመኪና ዓይነት እና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግሥታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከጋርዱላ ሁለገብ ኅ/ሥራ ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
  9. የጨረታውን ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይቻላል፡፡
  10. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣበት 15ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
  11. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- ጋርዱላ ዞን ግብርና መምሪያ ግቢ ውስጥ በስተግራ በኩል ይገኛል፡፡

ስ.ቁ :- 0939465386/0966487939/0952375403/0926234019

 

ጋርዱላ ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን

ጊዶሴ

Save Tender