በአ.ብ.ክ.መ የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በያዘው የግዥ ዕቅድ መሰረት ሎት-1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት-2 የኮምፕዩተርና ተዛማጅ ሎት-3 የጽዳት ዕቃዎች ሎት 4 የግንባታ ዕቃዎች ሎት-5 የመኪና ጎማዎች፣ ሎት-6 የውጭ ስሪት ፈርኒቸር፣ ሎት-7 የመኪና መለዋወጫ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በአ.ብ.ክ.መ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ጎዛምን ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
የ1ኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአ.ብ.ክ.መ የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በያዘው የግዥ ዕቅድ መሰረት ሎት-1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት-2 የኮምፕዩተርና ተዛማጅ ሎት-3 የጽዳት ዕቃዎች ሎት 4 የግንባታ ዕቃዎች ሎት-5 የመኪና ጎማዎች፣ ሎት-6 የውጭ ስሪት ፈርኒቸር፣ ሎት-7 የመኪና መለዋወጫ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ግዥ መጠናቸው 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈልና ገንዘብ ያዥ ላይ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ጎዛምን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር-10 ማግኘት ይችላሉ::
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለእያንዳንዱ ሎት ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) በማስላት በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል:: በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ-1 ገቢ አድርጐ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሲ.ፒ.ኦ ብሎ ማስገባት ይኖርበታል::
- የጨረታ መከፈቻ ቀኑን በተመለከተ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- ተጫራቶች በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድኑ ተዘጋጅቶ የተሠጣቸውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የይዘት ለውጥ ወይንም ማሻሻያ ሳያደርጉ ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል:: ሆኖም የተሠጠው ሰነድ ላይ የግልፅነት ማብራሪያ ካስፈለገ ደውለው ወይንም በአካል ቀርበው መጠየቅ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማቸውን በማድረግ፣ ማህተም በመርገጥና በፖስታ በማሸግና ፖስታው ላይ አድራሻ በመፃፍ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር -8 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መገለጫ /የተፈላጊነት ደረጃ/ በግዥ ቡድናችን ከተዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሠነድ ላይ ማየት ይችላሉ:: ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ግዥዎች የግዥ ቡድናችን የሚያቀርብ ይሆናል::
- ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት የጨረታ ውድድሩን በሎት ዋጋ (በጥቅል ዋጋ ድምር) የሚያወዳድር ይሆናል:: በርክክብ ወቅት በባለሙያ መረጋገጥ የሚገባቸው ዕቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ የምንረከብ ይሆናል::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፤
- ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር-8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም
በስልክ ቁጥር 0581780130/0587711422 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስ/ቡድን
ደብረ-ማርቆስ
