የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት መጽሔትና ብሮሸሮችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት እና ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጀው ሳምፕል መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መጽሔትና
ብሮሸሮችን ለማሳተም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/09/2017
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት መጽሔትና ብሮሸሮችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት እና ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጀው ሳምፕል መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፤ የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፤ የቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርትፊኬት (TIN) እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አ.ማ አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት አ.ማ ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር ብቻ) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንከ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል። ጨረታው ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል ፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ለተጨማሪ ማብራሪያ-
ስልክ 011470-90-95/0114-423608
ፋክስ 0114-421312
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
