በአህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ የደንብ ልብስ ተጠቃሚ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የደንብ ልብሶችን፣ የብረት ቆብ/ሄልሜት/ ... የመሳሰሉትን እንዲሁም የጽዳት እቃዎችን በዋጋ መሙያው ሰነድ ላይ ተለይቶ በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በነጠላ ዋጋ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በአህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡- አህስኮድሎ-01/132/17
በአህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ የደንብ ልብስ ተጠቃሚ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የደንብ ልብሶችን፣ የብረት ቆብ/ሄልሜት/ ... የመሳሰሉትን እንዲሁም የጽዳት እቃዎችን በዋጋ መሙያው ሰነድ ላይ ተለይቶ በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በነጠላ ዋጋ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃ ዘርፍ ላይ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የማንኛውም የግዥ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ከብር 20,000 ሺህ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት 15% ግማሹን /50%/ እና ከብር 10,000 ሺህ በላይ ግዥ ሲፈጸም ከተከፋይ ሂሳብ ላይ 2% ዊዘ ሆልዲንግ ታክስ ይቆረጣል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ዓይነት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአህስኮድ የምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት በደሴ ከተማ በአስተዳደርና ፋይናንስ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ የማይመለስ ለአንድ የጨረታ ሰነድ በብር 200.00 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አልቆ በ15ኛው ቀን ማግስት በአህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት/ደሴ ከተማ/ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፤ ተጫራቾች በእለቱ ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ያልተገኘ ተጫራችም በጨረታ ሂደቱ ተገዥ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደሩበትን የእቃ ዓይነት ስፔስፊኬሽን አይቶ በትክክል ዋጋ በመሙላት የሚጫረቱበትን ዋጋ በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ ደሴ ከተማ በሚገኘው በአህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት ግዥ ኦፊሰር ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ከማሸጊያው ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ፐርሰንት/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ቢያንስ ለ3ወር የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ሲታወቅ ላሸነፈው እቃ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /በcpo/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ቢያንስ ለ3ወር የሚቆይ በማስያዝ ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ ሙሉ ወጭ ተጫራቹ ችሎ የእቃውን ጥራት በተጠቃሚዎች በማረጋገጥ ጥራቱ ሲረጋገጥ ያሸነፈውን እቃ ደሴ ግብርና የሚገኘው ቅ/ጽ/ቤቱ መጋዘን ድረስ ገቢ ማድረግ ግዴታ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ማቅረብ እንዳለበት ተገንዝቦ ዋጋ መሙላትና መወዳደር ያለበት ሆኖ የሚሞላው የአንድ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በሚሸጠው ጨረታ ሰነድ ዋጋ መሙያ ፎርም መሰረት ቫትን ያካተተ መሆን ሲገባው በእስከርቢቶ ቫት ይጨመርበት ተብሎ ከተጻፈ ተጫራቹ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር በጥንቃቄ ይሞላ፡፡ በአጋጣሚ ስርዝ ድልዝ ከተፈጠረም ፓራፍ ይደረግ፡፡ ተጫራቾች እኩል ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ 1ኛ ብዛት ላሸነፈው ቅድሚያ ይሰጣል እንደዛም ሆኖ እኩል ከሆኑ በእለቱ በተገኙት ተጫራቾች ፊት በእጣ ይለያል፡፡ ተጫራች ካልተገኘም እጣው በኮሚቴው ይጣላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ሆኖ ተጫራቹ በዚህ ምከንያት ለሚያወጣው ወጪ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስ.ቁ 0331124973/0333111009 ይጠይቁ፡፡
አድራሻ ፡- ደሴ ካራ ጉቱ ግብርና ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮ ጽ/ቤቱ
አህስኮድ ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት
