Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ኬራቴ ከተማ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09-11-66-04-91
  • Website
  • Deadline19 Dec 2024, 2:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሣሪያና የፅዳት ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡-

  1. የጽህፈት መሣሪያና የፅዳት ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  ስለዚህ :-

  1. ከመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. በመንግሥት ግዥ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ መቅረብ የሚችሉ፣
  6. የጨረታ ዋስትና 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፣
  7. ጨረታውን ቢያሸንፉ ያሸነፏቸውን እቃዎችን ኬራቴ ከተማ በሚገኘው የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አምጥተው ማስረከብ የሚችሉ፡፡

ከሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ኬራቴ ከተማ በመገኘት ተጫራቾች ለጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፣ የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ-4 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው ከወጣ ከ15ኛው ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን 8፡30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 09-11-66-04-91/09-21-00-11-67

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender