Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የሚያገለግሉ የዘይት (Lubricants) እና የማለስለሻ ቅባት (Grease) ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡


የጨረታ  ማስታወቂያ

  ጨረታ  ቁጥር  EEP/GOP/NCB/10/2017

 

  1. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የሚያገለግሉ የዘይት (Lubricants) እና የማለስለሻ ቅባት (Grease) ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አቢሲኒያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 1ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከግዥ መምሪያ ህንጻ ምድር ቤት ጀነሬሽን ኦፕሬሽን ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን እቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GOP/NCB/10/2017 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦሪጂናል እና 1(አንድ) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ከዚህ በታች በተገለጸው ሰንጠረዥ መሰረት ለ90 ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንከ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንከ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ቁጥር

የግዥው ዓይነት

የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ስም

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት

ሎት-1

የዘይት (Lubricants) ግዥ

ለተለያዩ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች

ብር 150,000.00 (አንድ ሃምሳ ሺህ)

ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት

ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት

ሎት-2

ማለስለሻ ቅባት (Grease) ግዥ

ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ)

 

 

 

* ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

* ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 57 42 95/ 0115 58 19 16 መደወል ይችላሉ ፡፡

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

Save Tender