Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ብርሃን ሪጆ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር የጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን
  • Address ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ.ሜ ርቀት በደሴ መስመር ደ/ብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116320619
  • Website
  • Deadline18 Dec 2024, 5:15 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ብርሃን ሪጆ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር የጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን በ2017 በጀት አመት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እታዎች ሎት-1 ቋሚ እቃዎች ፈርኒቸር እና የቢሮ ማስዋቢያ ምንጣፍ፣ ሎት-2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት-3 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት-4 መለስተኛ ቋሚ /አላቂ እቃዎች/፣ ሎት-5 ህትመት ውጤቶችን፣ ሎት-6 የስፖርት ደንብ ልብስ፣ ሎት-7 የስፖርት ቁሳቁስ፣ ሎት-8 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ብርሃን ሪጆ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር የጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ብርሃን ሪጆ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር የጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን በ2017 በጀት አመት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት-1 ቋሚ እቃዎች ፈርኒቸር እና የቢሮ ማስዋቢያ ምንጣፍ፣ ሎት-2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት-3 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት-4 መለስተኛ ቋሚ /አላቂ እቃዎች/፣ ሎት-5 ህትመት ውጤቶችን፣ ሎት-6 የስፖርት ደንብ ልብስ፣ ሎት-7 የስፖርት ቁሳቁስ፣ ሎት-8 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ ፈቃድ ያላችሁ እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ::

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው፣ የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች (ፈርኒቸር) እቃዎች እና የቢሮ ማስዋቢያ ምንጣፍ፣ የጽዳት እቃዎች፣ መለስተኛ ቋሚ /አላቂ እቃዎች፤ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ህትመቶች የስፖርት ደንብ ልብስ እና የስፖርት ቁሳቁስ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን በጫጫ ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በአካል (በወኪሎቻቸው) አማካኝነት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በመንግስት የስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር 2% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ያስያዙበትን ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራች ሙሉ ስም፣ ፊርማ የድርጅቱን ማህተም፣ አድራሻ እና የግዥውን የእቃ አይነት/ሎት/ በመጥቀስ በጥንቃቄ ኦርጅናል ሰነድ እና የኦርጅናል ሰነዱን ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ እና በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ እና በጥንቃቄ በማሸግ በጫጫ ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ከቀኑ 11፡15 /አስራ አንድ ሰዓት ከሩብ/ ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 (አስራ አንድ ሰዓት ተኩል) ይታሸግና በማግስቱ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 (ሶስት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በጨረታ አከፋፈት ሥነ ሥርዓት ላይ ባለመገኘታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
  6. የጨረታ መክፈቻው በ16ኛው ቀን የበዓል ቀን (ቅዳሜና እሁድ) ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  7. በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 10,000 /አስር ሺ እና ለአገልግሎት 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈፀምለት ክፍያ ላይ 2% የቅድመ ግብር ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ቀንሶ ያስቀራል፡፡
  8. ማንኛውም ኮፒ የሚደረጉ ማስረጃዎች በትክክል መነበብ እና መታየት አለበት፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውለታ በመፈጸም የግዥውን አቅርቦት ጫጫ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ንብረት ከፍል ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግና በፍሎድ መደለዝ አይፈቀድም ምናልባት በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስህተት ቢፈጠር አንድ ሰረዝ አድርጎ ስለ መሰረዙ ፊርማ ማስቀመጥ አለበት።
  11. መስሪያ ቤቱ ግዥውን የሚፈጽመው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው መሠረት በጥቅል /በሎት/ ነው። አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩት የእቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፣
  12. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፡፡ ለወደፊቱም በመንግስት ግዥና ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ ያስያዙትም የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
  13. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅዕ ላይ በተገለፀው ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን መሰረት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ መገለፅ አለበት፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ (በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 0116320619 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ.ሜ ርቀት በደሴ መስመር ላይ ነው፡፡

 

 

በአብክመ  የደ/ብርሃን  ሪ/ፖ/ከ/አስ/ የጫጫ  ክ/ከተማ  አስተዳደር  ጽ/ቤት  ግዥ  ፋይናንስ  ቡድን

 

 

Save Tender