Tender Detail

Tender Details

  • Deadline09 Dec 2024, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Spare Parts

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ኮስሞቲከስ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ስፔር ፓርት በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ሞባይል እና የሞባል አክሰሰሪ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ስፔር ፓርት ዕቃዎች በሀራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 18/2017 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ኮስሞቲከስ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ስፔር ፓርት በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ሞባይል እና የሞባል አክሰሰሪ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ስፔር ፓርት ዕቃዎች በሀራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 18/2017 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ያለባቸው ሲሆን በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ለሀራጅ ጨረታ በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት፤ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ለምድቡ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እንዲሁም በሀራጅ ጨረታ ለወጡት ዕቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በጋላፊ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንከ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡

 

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

ግልጽ ጨረታ

እስከ 30/03/2017

30/03/2017 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል

2

ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

ሀራጅ ጨረታ

እስከ 30/03/2017

30/03/2017 ዓ.ም ግልጽ ጨረታ እንደተጠናቀቀ ሐራጅ ጨረታ ይጀመራል

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጂናል ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለባቸው ሲሆን፤ ይህን ባይፈጽሙ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን፤ ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርገው በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሱ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጡ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡፡
  4. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ ፡- 033 559 01 14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender