Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline31 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Water Well Drilling

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግቤ ቅ/ጽ/ቤት ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ ለማከናወን በዘርፍ የተሰማሩ እና የሥራ ልምድ ያላቸው ድርጅቶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሰረት አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


የግቤ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ ለማከናወን የወጣ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/08/2017

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግቤ ቅ/ጽ/ቤት ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ ለማከናወን በዘርፍ የተሰማሩ እና የሥራ ልምድ ያላቸው ድርጅቶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ቴክኒካል መስፈርት መሰረት አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ፡-

  1. ደረጃው GWWE 1 (አንድ) እና WWC 1 (አንድ) ተመጣጣኝ የብቃት ማረጋገጫ (የታደሰ) ያላቸው፤
  2. በዘርፍ የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ቲን፡ ቫት ከገቢዎች ሚ/ር ክሊራንስ/የምስክር ወረቀት፣ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ::
  3. ለውድድር የቀረቡት ተጫራቾች የብቃት/ቴከኒካል/ ሰነዶች ዋና ኦሪጂናል/ ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፡፡ ይህንን ማድረግ ያልቻሉ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ኦሪጂናል ህጋዊ ሰነዶችን (አግባብነት ያለው የ2017 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ እና ከሊራንስ) በመያዝ እና ለሚመለከተው ክፍል በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ ፋብሪካ አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት አ.ማ ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ120 ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል፡፡
  5. ከዚህ ቀደም ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውለታ ገብተው በውለታቸው መሰረት ሰርተው ያላስረከቡ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም ።
  6. ጨረታው የሚዘጋው ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል ፡፡
  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡-

የኢትዮጵያ  የግብርና  ሥራዎች  ኮርፖሬሽን

ስልክ 0114-42 36 08/0114-70 90 95

ፋክስ 0114-421312

አዲስ  አበባ  ኢትዮጵያ

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Save Tender