በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የፈረንጅ ጽድ ግንዶችና ሌሎችም እንጨቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የፈረንጅ ጽድ ግንዶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር GGWW/0010/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የፈረንጅ ጽድ ግንዶችና ሌሎችም እንጨቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾን የጨረታ ዋጋውን ከማቅረባቸው በፊት ፤የፈረንጅ ጽድ ግንዶችና ሌሎችም እንጨቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፋይናንስ ጽ/ቤት ትምህርት ጽ/ቤት ግብርና ጽ/ቤት ፣ጤና ጽ/ቤት፣ወጣቶችና ስፖርት ማእከል ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 10000 (አስር ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማስራት አለባቸው፡፡
- ስለአሻሻጡ የተዘጋጀ የፈረንጅ ጽድ ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን የፈረንጅ ጽድ ግንድ ሙሉ ክፍያ የጨረታ አሸናፊው በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ በመክፈል እቃዎችን መረከብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ፋይናንሻል ዶከመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
