በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ ለ2017 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የስፖርት ሜዳዎችና የጂምናዚየም ግንባታ ስራ በሁለት ደረጃ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት በቅድመ ብቃት ማረጋገጫ በሚቀርበው ፕሮፖዛል በመለየት ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 004/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ ለ2017 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የስፖርት ሜዳዎችና የጂምናዚየም ግንባታ ስራ በሁለት ደረጃ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት በቅድመ ብቃት ማረጋገጫ በሚቀርበው ፕሮፖዛል በመለየት ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥው አይነት ዝርዝር |
|
1 |
የስፖርት ሜዳ ግንባታ እና ጂምናዚየምን በመንግስትና የግል ባለሀብቶች ትስስር (Public Private Partnership) አጋርነት መሰረት አልምቶ ለመጠቀም የወጣ ጨረታ |
ማሳስቢያ
- ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡበትን፣ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃዎችና በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ /ዌብሳይት/ ላይ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል፤
- በቅድመ ብቃት ማረጋገጫው የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቫት /NAT/ ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፤
- ተጫራቾች በግንባታው ዘርፍ ያላቸውን ልምድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ደረጃ አምስት እና ከዚያ በላይ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች የግንባታ ስራውን ለማከናወን የሚያስችል በቂ ሰው ሀይል፣ ማሽነሪ ብዛት እና የተሟላ ኢንፍራስትራክቸር ያለው መሆኑን ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አሁን ላይ እየሰሩ ያሉትን የግንባታ ስራ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የውል ግዴታቸውን ለማጠናቀቅ ሚያስችል በቂ የገንዘብ አቅም እና መልካም አፈፃፀም እንዳላቸው የሚያሳይ ማስረጃ እና ባላቸው የስራ ልምድ ያንቀሳቀሱትን ገንዘብ የሚያሳይ ማስረጃ ከባንከ ማቅረብ አለበት፡፡
- በቅድመ ብቃት ውድድሩ በግል የሚያልፉ ድርጅቶች የመጫረቻ ሰነዱን በጋራ ወይም በሽርክና ማቅረብ አይችሉም፡፡
- በቅድመ ብቃት ውድድሩ በጋራ የሚያልፉ ድርጅቶች የመጫረቻ ሰነዱን በግል ማቅረብ አይችሉም፡፡
- በቅድመ ብቃት ውድድሩ ላይ የሚወዳደሩ የስፖርት ሜዳ ግንባታ እና ጂምናዚየም የማደራጀት ስራው ግንባታ ስራው ሊያጠናቅቁ የሚችሉበትን ጊዜ ገደብ ማስቀመጥ እለባቸው፡፡
- የጨረታ ጥሪው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀን ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዱን በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመ/ግዢ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 009 ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ቴክኒካል ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታዎች በማሸግ ኦርጅናል እና ኮፒ የሚል ምልክት /ፅሁፍ/ በማድረግ በአንድ ትልቅ ካኪፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
- በኦርጅናልና በቅጅው መካከል ያለመጣጣም ቢከሰት ኦርጅናል የበላይነት ይኖረዋል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ከተገለጸው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- የጨረታ ጥሪው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር የስራ ቀናት/ ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በቴክኒክ ኮሚቴው ይከፈታል፡፡
- ጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻው ቀን በበዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ የቅድመ ብቃት ማረጋገጫ ጨረታ ጥሪውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡
ማስታወሻ
- ይህ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ የጨረታ ሰነዱ አንድ አካል ተደርጐ ይቆጣጠራል፡፡
- አድራሻ ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ቢሮ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 6ኪሎ ከመድኃዓኒዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ :- 0118 28 29 52
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
