የጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የፍትህ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎትነት የሚጠቀምበትን ህንፃ ለማሳደስ ስለሚፈልግ በስራ ተቋራጭነት ተመዝግቦ የሚገኝና ከደረጃ 7-BC/GC እና ከዚያ በላይ ያሉ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የፍትህ ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የፍትህ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎትነት የሚጠቀምበትን ህንፃ ለማሳደስ ስለሚፈልግ በስራ ተቋራጭነት ተመዝግቦ የሚገኝና ከደረጃ 7-BC/GC እና ከዚያ በላይ ያሉ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የታደሰ ከግብር ውዝፍ ነፃ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ተጫራቾች ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ/ ብር በመክፈል ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ክፍል በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋስትና ማስከበሪያ 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር) በሲፒአ ወይም በባንከ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ግንባታውን የሚያከናውኑበትን ዋጋ ዋናውንና ኮፒ አንድ /1/ እና ካምፓኒ ፕሮፋይል ዋናውንና ኮፒ አንድ // ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ አስገብተው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በክልሉ ፍትህ ቢሮ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ከፍል ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር +251-475-51-11-68/+251-917-31-84-17 ይጠቀሙ፡፡
የጋም/ህ/ብ/ክ/ መንግስት የፍትህ ቢሮ
