በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምሥራቅ አዲስ አበባ ሪጅን በሥሩ ለሚገኙ ድንበኞች ኮንትራት ውል እድሳት አገልግሎት የሚውል የ2017 በጀት ዓመት የኮንትራት ፋይል ውል ማቀፊያ 240 ግራም 35*25 ሳ.ሜ እና የደንበኛ ውል ኮፒ 80 ግራም 35*25 ሳ.ሜ መጠን በድርጅቱ አርማ የሆነ ፉል ከለር ከፊትና ከኋላ የውል ጽሁፍ ህትመት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ፡ ምሥ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/001/2017 (ሎት-2)
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምሥራቅ አዲስ አበባ ሪጅን በሥሩ ለሚገኙ ድንበኞች ኮንትራት ውል እድሳት አገልግሎት የሚውል የ2017 በጀት ዓመት የኮንትራት ፋይል ውል ማቀፊያ 240 ግራም 35*25 ሳ.ሜ እና የደንበኛ ውል ኮፒ 80 ግራም 35*25 ሳ.ሜ መጠን በድርጅቱ አርማ የሆነ ፉል ከለር ከፊትና ከኋላ የውል ጽሁፍ ህትመት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
|
ሎት |
ኮንትራት ፋይል ማቀፊያ 240 ግራም 35*25 መጠን የሆነ በውስጥ የውሉ ፅሁፍ ህትመት እና የደንበኛ ፋይል ኮፒ 80 ግራም በጀርባው እና በውስጡ ያለው የጽሁፍ ህትመት ሥራ መጠን 35*25cm በድርጅቱ አርማ ሙሉ ከለርድ ህትመት |
ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት |
ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት |
49,000.00 (አርባ ዘጠኝ ሺህ ብር) |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ፣ የግብር ከፋይ መ/ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ድህረ- ገፅ ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት 2 ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ EEU-EAAD AACC (1000298392902) ገቢ በማድረግ የባንክ እስሊፕ በማስገባት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ:- ኮተቤ ብረታብረት ፊት ለፊት በሚገኘው በምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን የሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት የንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 14፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ላይ በማድረግ «አሪጅናል እና ኮፒ» በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ምሥ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/001/2017 ሎት2 የሚል ምልክት በማድረግ ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን በሰም ያልታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ሳይከፈት ውደቅ ይደረጋል፡፡ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር +251-011-667-58-77/0116-67 50 75 መደወል ይችላሉ፡፡
- ሪጅኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
አዲስ አበባ
