በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት አማካኝነት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት አማካይነት ለሚሰራው የደመካሽ ድልድይ ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር GGWW/0011/2017
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት አማካኝነት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት አማካይነት ለሚሰራው የደመካሽ ድልድይ ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቶች:-
- የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት/ መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀልአምባ ከተማ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/RC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጮች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ብቻ በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው ::
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶከመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት መሀልአምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር -03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ በ21ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ማሳሰቢያ ፡-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም፡፡
- በወረዳው ውስጥ ፕሮጀከት ይዞ ስራውን ያልጨረሰ ተጫራች መወዳደር አይችልም ::
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልክታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
ለበለጠ መረጃ ፡- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ
ስልክ ቁጥር ፡- 0113360162/146 ይደውሉ
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
መሀል አምባ
