በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የኮ/ቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለመምሪያና እና ለክፍለ ከተሞች ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳርያ የጽዳት እቃ፤ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሌሎች አላቂ እቃዎች፤ ፈርኒቸር፤ የመኪና እና እና የመኪና ዘይቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የኮ/ቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የኮ/ቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለመምሪያና እና ለክፍለ ከተሞች ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳርያ የጽዳት እቃ፤ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሌሎች አላቂ እቃዎች፤ ፈርኒቸር፤ የመኪና እና እና የመኪና ዘይቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ
ሎት 2. የጽዳት እቃ
ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች አላቂ እቃዎች
ሎት 4. ፈርኒቸር
ሎት 5. የመኪና እቃ እና የመኪና ዘይቶች
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ።
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
- የግዥ መጠኑ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል ከዚህ በታች ከሆነ ህጋዊ ደረሰኝ ሊኖራቸው ይገባል።
- በጨረታው ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1- 5 ላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-5 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ኮ/ቻ ከተማ አስ/ፖሊስ መምሪያ ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 410 4ኛ ፎቅ በመምጣት ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት 11፡00 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና 2% በየሎቶቹ ለየብቻ በመለየት በሲፒአ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
- የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በሎት ወይም በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥም መ/ቤት ጨረታ ካወጣው አካል ከጨረታው መክፈቻ ከ5 ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0333517640 ደውሎ መጠየቅ ይችላል። በመሆኑም በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሎቶቹ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮ/ቻ ከተማ አስ/ፖሊስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 410 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚጠናቀቅበት ቀን 4፡00 ሰአት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚህ ሰአት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታ በግልጽ ይከፈታል ነገር ግን የጨረታው ቀን በአል ከሆነ እና የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን እና ሰአት የሚከፈት ይሆናል ።
- የማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለበትም ።
- አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን መ/ቤቱ ንብረት ክፍል አሰናአገር ክ/ከ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 033351764070
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የኮ/ቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ
