Tender Detail

Tender Details

  • Company አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Address ከፓስተር ወረድ ብሎ ወደ ጨው በረንዳ በሚወስደው መንገድ ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 400 ሜትር ርቀት ላይ ወረዳ 6 አስተዳደር ግቢ ውስጥ ሁለተኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2-73-58-85
  • Website
  • Deadline04 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 ክልል ውስጥ የሚገኘው የወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2017 ዓ.ም 2ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ እቃዎችን በጨረታ እወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት


2ኛ  ዙር  አስቸኳይ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የግዥ  ጨረታ  መለያ  ቁጥር :- አዲስ/ክ/ከ/ወ6/347/2017

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 ክልል ውስጥ የሚገኘው የወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2017 ዓ.ም 2ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ እቃዎችን በጨረታ እወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 የደንብ ልብስ — 6800 ብር

ሎት 2. የፅህፈት መሳሪያዎች — 1440.00 ብር

ሎት 3. የህትመት — 10,000 ብር

ሎት 4. ትራንስፖርት — 20,000 ብር

ሎት 5. መስተንግዶ — 60,322.40 ብር

ሎት 6. የቋሚ እቃዎች — 60,000.00 ብር

ሎት 7. ሌሎች አላቂ አቃዎች — 10,000.0 ብር

ሎት 8. ጥገና — 12,000.00 ብር

ሎት 9. ዲኮርና ሞንታርቦ ኪራይ — 2000.00 ብር

ሎት 10. የፅዳት አቃዎች — 2000.00 ብር

ተጫራቾች ከሚጫረቱበት እቃ ጋር ግንኙነት ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው በጨረታው ተካፋይ መሆን እንደሚችሉ የሚያመለክት ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የአቅራቢ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት ከሚጫረታቸው ሰነዶች ጋር አባሪ መሆን ይኖርበታል። የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ሰነዱን ቢሮ 2ኛ ፎቅ ላይ ፋይናንስ ፅ/ቤት በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ለፋይናንስ ፅ/ቤት ቼክ ማስያዝ ይኖርበታል።
  2. የጨረታው ሰነድ ሲገባ ናሙና አብሮ መቅረብ አለበት ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡበት ሰነድ ዋናውና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።
  3. ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ከመስሪያ ቤታችን ጋር ውል ተዋውሎ የውል ማስከበሪያ ዋጋውን 10% ዋጋ ማስያዝ ይኖርበታል፤ በተጨማሪ የአሸናፊውን እቃ በ10 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ግዴታ አለበት ይህ ባይሆን ግን ለጨረታው የተያዘውን ቼክ ዋጋ በቀጥታ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል።
  4. ጨረታው በ3ኛው ቀን በ4፡00 ሰአት ይዘጋል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰአት ይከፈታል።
  5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
  6. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ አካላት በሀገር ውስጥ ምርት ላይ ብቻ መወዳደር ከፈለጉ ህጋዊ ማስረጃ ሲያቀርቡ ሰነድ ወስደው መወዳደር ይችላሉ።
  7. በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  8. ጽ/ቤቱ ከውል በፊት 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ ከውል በኋላ 25% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  10. አሸናፊው ያሸነፈባቸውን ንብረቶች የወረዳው ንብረት ከፍል ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች የአንዱ ነጠላ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ አለበት፡፡ ያልተጠቀሰ ከሆነ ቫት (እንዳካተተ ) ተደርጎ ይወሰዳል ።
  12. እያንዳንዱ ተጫራች ለሚያስገባው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።

አድራሻ ፡- ከፓስተር ወረድ ብሎ ወደ ጨው በረንዳ በሚወስደው መንገድ ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 400 ሜትር ርቀት ላይ ወረዳ 6 አስተዳደር ግቢ ውስጥ መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ :- ስልክ  ቁጥር 011-2-73-58-85 ወይም 0112-77-48-00

በአዲስ  ከተማ  ክፍለ  ከተማ  ወረዳ  6  አስተዳደር  ፋይናንስ  ጽ/ቤት

Save Tender