የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቅ/ፅ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡
ADDIS ABABA HOUSING DEVELOPMENT CORPORATION (የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- ደቡብ ቅ/ጽ/ቤት/001/2017
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቅ/ፅ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል
|
ሎት |
የእቃው / የአገልግሎቱ አይነት |
ማብራሪያ |
|
ሎት 1 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የፕሪንተር ቀለም |
|
|
ሎት 2 |
የሰራተኞች የደንብ ልብስ |
|
|
ሎት 3 |
የጽዳት ዕቃዎች |
|
|
ሎት 4 |
የተሽከርካሪ ጌጣጌጥና የመኪና ጎማ |
|
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በዚህም መሰረት የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/: የታደሰ ሊብሬ እና በሶስተኛ ወገን የመድን ዋስትና ኢንሹራንስ ማሟላት እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሎት 1 - 5,000 (አምስት ሺህ ብር)፤ ለሎት 2 - 6,000 (ስድስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 3 – 2.000 (ሁለት ሺህ)፤ ለሎት 4 – 6,000 (ስድስት ሺህ) በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ሲሆን ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ቅ/ጽ/ቤቱ ከክፍያና ፋይናንስ ቡድን በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን በግልጽ መለየት አለባቸው፡፡ በግልፅ ካልተለየ የቀረበው ዋጋ ከቫት ጋር ነው ተብሎ ይወሰዳል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡40 ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ክፍል ይከፈታል።
- የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ/ ከተዘጋ በኋላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫራቱበትን አገልግሎት የአንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በመለየት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ቅ/ጽ/ቤቱ በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ካራ ቆሬ በረጵ ትምህርት ቤት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ አጃንባ ሳይት ውስጥ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 09-66-42-82-98/09-12-00-72-07/ 09-82-10-37-15 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
