አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት canon SD ካሜራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Amhara Road Works Enterprises (ARWE) (የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር - አመስድ 08/2017
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት canon SD ካሜራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይንም በዘመኑ የተሰጠ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው እና የሞሉት ዋጋ ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ተጫራቾች በድርጅታችን ስም የተሰራ ማለትም በአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ወይም AMHARA ROAD WORKS ENTERPRISE በሚል የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 36,000 ብር (ሰላሳ ስድስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ያለ ቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ዋስትና ከጨረታ ዶክመንቱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ15ኛው ቀን 9:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 09:30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ወይም የበአላት ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የካሜራው ዝርዝር ስፔሲፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 058-320-35-76 መደወል ይችላሉ፡፡
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት
ባህር ዳር
