Tender Detail

Tender Details

  • Deadline16 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች እና በሎት 2 የጽዳት እቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።


የጨረታ  ማስታወቂያ

   ጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/13/2017

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች እና በሎት 2 የጽዳት እቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድህረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው::
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግባት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነድ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ፤ በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
  4. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር 9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የፅህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/13/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ሎት

Description

 

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ

 

የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት

 

1

የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ

 

ብር 185,000.00 (አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ብር)

 

ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

 

 

ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

 

2

የጽዳት ዕቃዎች ግዥ

 

ብር 185,000.00 (አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ብር)

 

  1. ተጫራች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 011 558-06-27 መደወል ይችላሉ።
  2. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ  ኃይል

Save Tender