የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የአሸዋ ፣ 02 ጠጠር ግንብ ድንጋይ እና 00 ጠጠር ከነትራንስፖርቱ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 11/2017 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት አሸዋ 02 ጠጠር ግንብ ድንጋይ እና 00 ጠጠር ከነትራንስፖርቱ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የአሸዋ ፣ 02 ጠጠር ግንብ ድንጋይ እና 00 ጠጠር ከነትራንስፖርቱ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 11/2017 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት አሸዋ 02 ጠጠር ግንብ ድንጋይ እና 00 ጠጠር ከነትራንስፖርቱ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለአሸዋ፤ ግንብ ድንጋይ እና 02 ጠጠር ከነትራንስፖርቱ ግዥ ለእያንዳንዱ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) እና ለ00 ጠጠር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼከ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ጋራንቲና (un conditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የኮንስትራክሽን ዲዛይን ፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ስልክ ቁጥር 0114621457
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
