Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
  • Address ምስራቅ ጎጃም ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0587760443
  • Website
  • Deadline16 Dec 2024, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electronics Materials

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ማለትም የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁስ፤ የጽ/መሳሪያ የጽዳት እቃዎች ፡ ኤሌክትሮኒክስ አቃዎች፤ ግንባታ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ያምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት


ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ  ቁጥር 01/2017

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ማለትም የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁስ፤ የጽ/መሳሪያ የጽዳት እቃዎች ፡ ኤሌክትሮኒክስ አቃዎች፤ ግንባታ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ያምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

    1. የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
    2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
    3. የዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
    4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም የማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
    5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100 /መቶ/ የኢትዮጵያ ብር ለሚወዳደሩበት ሰነድ በመግዛት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 መውሰድ ይችላሉ፡፡
    6. ተጫራቾች የተጠየቁትን እቃዎች በተጠየቀው ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሙላት ያለባቸው ሲሆን የስፖርት ትጥቆች እና ሳምፕል ከቀረበላቸው እቃዎች መስ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ይሆናል።
    7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ ብር /የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ፤ የጽ/መሳሪያ 10,000፣ የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁስ ብር 10,000 ኤሌከትሮኒከስ እቃዎች 5000 የጽዳት እቃዎች ብር 2000 የግንባታ እቃዎች ብር 10,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሰ.ፒ.አ /ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
    8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈራረም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡30 ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ አለት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 /አራት ሰዓት/ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻለው እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ብቻ ነው፡፡
    9. የጨረታ መክፈቻ ቀን ዝግ /በዓል/የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
    10. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሎት የሚያወዳድር ስለሆነ በአንድ ምድብ ውስጥ ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ ሳይሞሉ መተው አይቻልም በሎት ያልሞላ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
    11. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው::
    12. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት በተገለፀላቸው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርበው ውል መያዝ አለባቸው፡፡
    13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
    14. የጨረታው ተሳታፊዎች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር 0587760443 መደወል ይችላሉ፡፡

 

በአማራ  ብሄራዊ  ክልላዊ  መንግስት  በምስ/ጎጃም  ዞን  የደጀን  ወረዳ  ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

Save Tender