Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline16 Dec 2024, 2:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Engineering Consultant

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎ ተርሚናል 1 G + 2 ቢሮ ህንጻ እድሳት እና G+4 ሁለገብ ግንባታ ህንጻ ፕሮጀክት ዲዛይን ግምገማ፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት የሚሰጡ በደረጃ-1 ጠቅላላና የህንጻ ሥራ አማካሪነት የሀገር ውስጥ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


የጨረታ  ማስታወቂያ

 የጨረታ  ቁጥር:- SSNT-T504

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎ ተርሚናል 1 G + 2 ቢሮ ህንጻ እድሳት እና G+4 ሁለገብ ግንባታ ህንጻ ፕሮጀክት ዲዛይን ግምገማ፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት የሚሰጡ በደረጃ-1 ጠቅላላና የህንጻ ሥራ አማካሪነት የሀገር ውስጥ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ የሆኑ ኣማካሪዎችን ሥራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  • ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  • የፕሮጀከቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ 150 ተከታታይ ቀናት ለG+2 የካርጎ ቢሮ ግንባታ እድሳት ማስፋፊያ እና 300 ተከታታይ ቀናት ለ G + 4 ሁለገብ ህንፃ ግንባታ ነው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T504 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢ-ሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አንድ መቶ ሺህ ብር (100,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታውን የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።
  • ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር ፡- 011-517-8918

ኢ-ሜይል ፡- EskedarG@acthiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

Save Tender