የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ የጎርፍ መከላከል ስራ ጥናት፣ ዲዛይን፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር የምክር አገልግሎት የሚሰሩ ደረጃ አንድ በውሀ ሀብት ምህንድስና የማማከር ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- SSNT-T509
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ የጎርፍ መከላከል ስራ ጥናት፣ ዲዛይን፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር የምክር አገልግሎት የሚሰሩ ደረጃ አንድ በውሀ ሀብት ምህንድስና የማማከር ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ
- በአገልግሎቱ ዘርፍ ለ2015/2016 ዓ.ም ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ እና የTIN ምዝገባ ወረቀት ያለው VAT ተመዝጋቢ የሆነ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2015/2016 ዓ.ም የታደሰ ደረጃ አንድ በውሀ ሀብት ምህንድስና የማማከር ፍቃድ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T509 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሁለት መቶ ሺህ ብር (200,000) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለበት። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና የሚቀርብ ቅድመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ታህሳስ 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
አሊ አስፋው
ስልክ ቁጥር: 011-517-4552
ኢ-ሜይል: AliAs@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
