Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Camera

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት በኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር በ2017 በጀት አመት በተያዘው ለመምሪያው አገልግሎት የሚውል የቋሚ ዕቃ ማለትም Drone Camera በግልጽ ጨረታ በማውጣት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት በኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር በ2017 በጀት አመት በተያዘው ለመምሪያው አገልግሎት የሚውል የቋሚ ዕቃ ማለትም Drone Camera በግልጽ ጨረታ በማውጣት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ::

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
  3. የግዥ መጠን ብር 200.000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በመሄድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት 11፡30 ሰዓት ድረስ ከ19/03/2017 ዓ.ም እስከ 03/04/2017 ዓ.ም ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 3,825/ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ አምስት ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን /ሲ.ፒ.ኦ/ ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
  8. የቋሚ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር /ብቻ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይቻላል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት 04/04/2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ እለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተጫራቾች ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው ጊዜ የባዕል ቀን ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
  11. በጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባችኃል፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲገጥማችሁ አሰሪው መ/ቤት ጨረታውን ካወጣው አካል ከጨረታው መክፈቻ እለት በፊት በስልክ ቁጥር 033-351-10-42 / 09-75-42-90-82 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. ጨረታው ለ40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  14. የጨረታው ውድድር በጠቅላላ ዋጋ ሎት ድምር ነው፡፡
  15. መምሪያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

Save Tender