Tender Detail

Tender Details

  • Deadline06 Dec 2024, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ ዕቃዎችና ተሽከርካሪዎች በሐራጅና ግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ/04/2017 ዓ.ም ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ ዕቃዎችና ተሽከርካሪዎች በሐራጅና ግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ/04/2017 ዓ.ም ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

ዘርፍ

የጨረታው ዓይነት

እቃው ያለበት ቦታ

1

ኮስሞቲክሶች

ግልጽ ጨረታ

በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ እቃ መጋዘን

2

ተሽከርካሪ

ግልጽ ጨረታ

በሚሊ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ውርስ እቃ መጋዘን

3

የተዘጋጁ ልብሶችና ብትን ጨርቅ (printed lady dress material)

ግልጽ ጨረታ

በሚሊ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ውርስ እቃ መጋዘን

4

ጫማዎች

ግልጽ ጨረታ

በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ እቃ መጋዘን

5

የቤትና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች

ግልጽ ጨረታ

በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ እቃ መጋዘን

6

ምግብ ነክ ዕቃዎች

ግልጽ ጨረታ

በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ እቃ መጋዘን

7

ህንጻ መሳሪያ ዕቃዎች

ግልጽ ጨረታ

በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ እቃ መጋዘን

8

ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ግልጽ ጨረታ

በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ እቃ መጋዘን

9

ኮስሞቲክሶች

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ እቃ መጋዘን

10

የመኪና መለዋወጫ (Spare Parts)

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ እቃ መጋዘን

11

ልዩ ልዩ ዕቃዎች

ሐራጅ ጨረታ

በሰመራ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ እቃ መጋዘን

በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-

  1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ስብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም:: በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መከፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ለተሽከርካሪዎች ግልጽ ጨረታ ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መጫረት ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00-5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 30 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ኮስሞቲክስ ዕቃዎች ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) የልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች (Spareparts) (ምድብ 01) ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች (Spareparts ምድብ 02) ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የግል ባንክ ከሆነ ከሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ከሆነ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ቅርንጫፎች፤ ከሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

ግልጽ ጨረታ

እስከ 26/03/2017

27/03/2017 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 3፡45 ሰዓት ይከፈታል

2

ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

ሐራጅ ጨረታ

እስከ 26/03/2017

27/03/2017 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

 

  1. የጨረታው መከፈቻ ቦታ:- በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
  2. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጽ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ግቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡፡
  4. ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው::
  5. ለተሽከርካሪ ስመ ንብረት ዝውውር የሚወጡ ወጭዎችን የጨረታ አሸናፊው አካል የሚሸፍን ይሆናል።
  6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ለተጨማሪ መረጃ በስቁ፣-0333662302/0333665004 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

ሰመራ  ጉምሩክ  ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት

Save Tender