Tender Detail

Tender Details

  • Company በምሥራቅ ወለጋ ዞን የዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
  • Address ወለጋ ፡ ኦሮሚያ ክልል፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-17-81-65-37
  • Website
  • Deadline16 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Equipment And Machinery

በምሥራቅ ወለጋ ዞን የዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ሥር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለህንፃ መሣሪያዎች ከዚህ በታች ያለውን ምዘናዎችን ከሚያሟላ አቅራቢ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በምሥራቅ ወለጋ ዞን የዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በምሥራቅ ወለጋ ዞን የዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ሥር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለህንፃ መሣሪያዎች ከዚህ በታች ያለውን ምዘናዎችን ከሚያሟላ አቅራቢ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. የ2016 ዓ/ም የንግድ ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ የንግድ ዘርፍ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የቫት ስሌቱን አብሮ ሠርቶ ማቅረብ የሚችሉና ቫቱ ካልተጨመረበት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን መረዳት የሚችሉ።
  4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ /ቢድ ቦንድ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) 10000 (አስር ሺህ) ማስያዝ የሚችሉ።
  6. ደረጃውንና ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ በጊዜ ማቅረብ የሚችሉ።
  7. አስተማማኝና ጥራት ለሌላቸው ዕቃዎች ተጠያቂነትን የሚወስዱ
  8. አንዱ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ በ% ተንተርሶ ዋጋ መቀነስም ሆነ መጨመር የማይቻል መሆኑን የሚያውቁ
  9. ተጫራቾች እስከ ከ7/4/2017 ዓ/ም ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ለዋዩ ቱቃ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመንግሥት የሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ ፡፡
  10. ተወዳዳሪዎች የተጠየቁትን ማስረጃ በሙሉ ኦርጂናሉንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ ስሙን፣ ስልኩን፣ አድራሻውን ጽፎበትና የድርጅቱ ማሕተም አድርጎበት ሁለቱን በአንድ ትልቅ በሰም በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በ7/4/2017 ዓ/ም ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ7/4/2017 ዓ/ም ተወዳዳሪዎች ፣ ወኪሎቻቸው ወይም እነርሱ በሌሉበትም ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ውድድሩ ይካሄዳል።
  11. ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ካሸነፉ ከታወቀ ባንከ (ኢንሹራንስ) 10% ፕርፎርማንስ ቦንድ በማቅረብ ያሸነፉትን ዕቃዎች በሙሉ እስከ ዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ ለማምጣት የሚገደዱ ይሆናል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ ስልክ ቁጥር-

09-17-81-65-37/09-17-88-91-38/0913301411

 

በምሥራቅ ወለጋ ዞን የዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

Save Tender