በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስ/ ገንዘብ መምሪያ በደሴ ከተማ የሚገኘው ቁጥር 1 የህዝብ ቤተ መጽሐፍት የጥገና ስራ ለማሰራት ደረጃቸው BC/GC 7 እና በላይ የሆኑ ሥራ ተቋራጮች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
ግልጽ የብሔራዊ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 002/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስ/ ገንዘብ መምሪያ በደሴ ከተማ የሚገኘው ቁጥር 1 የህዝብ ቤተ መጽሐፍት የጥገና ስራ ለማሰራት ደረጃቸው BC/GC 7 እና በላይ የሆኑ ሥራ ተቋራጮች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ድርጅትዎ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘርፉ የተሰማሩና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ የሚችል፡
- በዚሁ ስራ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፤
- B S እና GC ደረጃ 7 እና በላይ የሆነ፤
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ /ሰፕላይ ሊስት/ ላይ የተመዘገቡ፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-5 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ደሴ ከተማ ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ 200.00 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 2017 ዓ/ም ደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን የጠቅላላ ዋጋውን 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረት የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት የግንባታ ማቴሪያል ከማስገባቱ በፊት በቦታው ተገኝቶ ስለስራው አጠቃላይ አሰራር ከባለሙያዎች ጋር ምክክር ማድረግ መቻል ይኖርበታል ።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለት ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር እስከ 22ኛው ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት ኦሪጂናል እና የማይመለስ ኮፒ የሥራ ፈቃድ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ይዘው በቀረቡበት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ደሴ ከ/አስ/ገ/መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 11 የተጠቀሰው ቢኖርም ተጫራቾች በአካል ባይገኙመ ጨረታው ከመከፈት አያግደውም።
- ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሆኖ ለመለየት አሻሚ ነገር መኖር የለበትም
- የጨረታ መክፈቻው ቀን በዕለቱ ከሥራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የሻለ ዘዴ ካገኘ ጨታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0331118629 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስ/ ገንዘብ መምሪያ
