በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደሴ ከተማ አስ/ ገንዘብ መምሪያ ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በደሴ ከተማ ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ከዚህ በታች በተዘረዘረው ምድብ መሰረት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
ግልጽ የብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደሴ ከተማ አስ/ ገንዘብ መምሪያ ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በደሴ ከተማ ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ከዚህ በታች በተዘረዘረው ምድብ መሰረት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ምድብ 1 ቋሚ እቃዎች፣
- ምድብ 2 መኪና እቃዎች፣
- ምድብ 3 የላብራቶሪ እቃዎች፣
- ምድብ 4 የተማሪዎች መጽሐፍ፣
- ምድብ 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
ግዥ ለመፈፀም ጨረታ ለማጫረት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ድርጅትዎ የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልቶ መወዳደር እንዲችል ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
- ግዡ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢነት የተመዘገቡ
- ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ በሎት ነው ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-5 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ደሴ ከተማ ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ 200 ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 1.5 % በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባችኋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የመወዳደሪያ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 በደሴ ከተማ ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዛወራል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0331118629 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደሴ ከተማ አስ/ ገንዘብ መምሪያ
