Tender Detail

Tender Details

  • Company በድሬዳዋ አስተዳደር የመልካ ጀብዱ ጤና ጣቢያ
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 025-116-00-00
  • Website
  • Deadline09 Dec 2024, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Laboratory Equipment And Chemicals

በድሬዳዋ አስተዳደር የመልካ ጀብዱ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መድሃኒትና ላብራቶሪ ሪኤጀንቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር የመልካ ጀብዱ ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

በድሬዳዋ አስተዳደር የመልካ ጀብዱ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መድሃኒትና ላብራቶሪ ሪኤጀንቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

* የመድሃኒት ግዥና

* የላብራቶሪ ሪኤጀንት ግዥ

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከድሬዳዋ አስተዳደር መልካ ጀብዱ ጤና ጣቢያ ግዥና ንብረ/አስ/ ክፍል ቁጥር 7 በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋ የያዘውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቭሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ቀናት በኋላ /በ16ኛው የስራ ቀን/ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀውና በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. የተከፈለበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  2. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት
  3. የዘመኑን ግብር የከፈለበት የምስክር ወረቀትና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. አንድ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መቀነስም ሆነ መጨመር የማይችል መሆኑን።
  5. በጨረታው ለተሸነፉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን የአሸናፊዎች ግን መ/ቤቱ ጋር ውል ሲፈጽሙና የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲያሲዙ ብቻ የሚመለስ ይሆናል።
  6. የጨረታ አሸናፊዎች በ10 ቀን ውስጥ ቀርበው ውል ባይፈጽሙ የውል ማስከበሪያ ባያሲዙ የጨረታው አሸናፊነታቸው ተሰርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ የሚወረስ መሆኑን እናሳውቃለን።
  7. የጨረታው ሳጥኑ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጨምሮ ከ15 ቀናት በኋላ (በ16ኛው የስራ ቀን ከሆነ) ከጠዋቱ በ3፡30 ይታሸጋል።
  8. ጨረታው በ16ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ በግዥ ፋይ/ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የባንክ በተረጋገጠ CPO ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያ መሰረት የመጫረቻ ሰነዱን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በትክክል መሙላትና መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጤና ጣቢያው ግዥውን ለመፈጸም የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 025-116-00-00 ወይም 0913919736 - ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በድሬዳዋ አስተዳደር የመልካ ጀብዱ ጤና ጣቢያ

Save Tender