Tender Detail

Tender Details

  • Company የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን
  • Address ድሬዳዋ ቀበሌ 03 ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0251124892
  • Website
  • Deadline08 Dec 2024, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Water Pipes And Fittings

የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለ2017 በጀት ዓመት የቧንቧ መገጣጠሚያዎች (pipe fitting) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።


በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን 2017 በጀት ዓመት የቧንቧ መገጣጠሚያዎች (pipe fitting) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

      • ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት መወዳደሪያ ኤንቨሎፑ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
      • የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከግዥ ፋይናንስና ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
      • የጨረታ ሰነድ በውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 05 130 ሰዓት እስከ 1130 ሰዓት ዘወትር በስራ ሰዓትና ቀን መግዛትና ማስገባት ይቻላል።
      • ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን 300 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሣሣይ ቀን 330 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
      • ተጫራቾች ብር 35,000.00 /ሰላሳ አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ዶክመንቱ ሲከፈት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
      • የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪ በጨረታ ዶከመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው በሁለት ኮፒ መቅረብ አለባቸው።
      • ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን እቃ የግዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በእስፔስፊኬሽኑ እና በናሙናው መሠረት 30 ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በሚገኝበት መጋዘን አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡
      • በዶክመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ወይም ሳምፕል ወጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም፡፡
      • የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈው ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና /CPO/ ወይም በሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችል፡፡
      • በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግሥት ግዢ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።
      • ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ ጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም።
      • ባለስልጣን /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
      • አድራሻ፡- ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ቀበሌ 03 ድሬዳዋ ስልክ ቁጥር 025 112 48 92 79 ...446

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባስሥልጣን

 

Save Tender