Tender Detail

Tender Details

  • Deadline11 Dec 2024, 10:15 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Medical Equipment And Supplies

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለመካከለኛ ክሊኒክ አገልግሎት የሚውል የመድሀኒትና የህክምና መገልገያ ግብዓቶችን ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕግ/25/02/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ  ማስታወቂያ

    ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕግ/25/02/201

  1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለመካከለኛ ክሊኒክ አገልግሎት የሚውል የመድሀኒትና የህክምና መገልገያ ግብዓቶችን ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕግ/25/02/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
  2. ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚያገለግል መካከለኛ ክሊኒክ አገልግሎት የሚውል የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ ግብዓቶች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የግዥ መመሪያ መሠረት ሲሆን ተጫራቾች ከሚፈለገው ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  4. የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ወይም ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 /ሀያ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 201 ይከፈታል።
  6. ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ ግብዓት ግዥውን በኮርፖሬሽኑ መካከለኛ ከሊኒከ ቅጥር ግቢ ያስረከባል።
  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 011-855-36-17

የፖስታ ሣ.ቁ./P.O. Box 299

 

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

Save Tender