በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሀረር ፌዴራል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታልና አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (22-02B) የተለያዩ ዲያሜትሪ ያላቸውን PPR (PN20) Fitting, UPVC PN-6 Pipes Fitting flooring draing Vulcanite Pipes for chemical wastes & Class-B galvanized steel fine water pipes and Fitting ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- መኮኢ/ፕሮ/22-02B/04/2017
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሀረር ፌዴራል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታልና አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (22-02B) የተለያዩ ዲያሜትሪ ያላቸውን PPR (PN20) Fitting, UPVC PN-6 Pipes Fitting flooring draing Vulcanite Pipes for chemical wastes & Class-B galvanized steel fine water pipes and Fitting ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም :-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ ታክስ ክሊራንስ (tax clearance) ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በቅድመ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ ሀረር ፌዴራል ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የሀረር ፌዴራል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አስተዳደርና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የ Sanitary Material ዕቃ ናሙና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኃላ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም 9:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሀረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሀረር ፌዴራል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀከት የግዥ እና አቅርቦት ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በሐረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራከሽን
ኢንተርፕራይዝ የሐረር ፌዴራል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀከት።
ስልክ ቁጥር :- 025-4-66-70-13/025-4-66-43-59/09-17-81-96-26
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የሐረር ፌዴራል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት
